Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ከተሳተፉት ሶስት አትሌቶች ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል

በአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ከተሳተፉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በመጀመሪያው ምድብ የወርቅውኃ ጌታቸው 2ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍፃሜ ማለፍ ስትችል መቅደስ አበበ በሁለተኛው ምድብ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍጻሜ ማለፏን አረጋግጣለች፡፡ በሶስተኛው ዙር የተሳተፈችው ሲምቦ አለማየሁ 5ኛ ደረጃን ይዛ ርቀቱን በመጨረሷ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች። ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን…
Read More...

በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጀመሪያ ቀን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገኑ 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ማጣሪያ ውድድሮች በወንዶች 3,000 ሜትር መሠናክል እና በሴቶች የ1,500 ሜትር ውድድሮች ስድስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በብቃት አልፈዋል። 3,000 ሜትር መሠናክል ወንዶች፣ ጌትነት ዋለ 8:17.49፣ ለሜቻ ግርማ 8:19.64 እና ኃ/ማርያም አማረ 8:18.34…

ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዮርዳኖስ ዓባይ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ክለቡ አስታወቀ፡፡ ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ተከትሎ÷ አሰልጣኝ ዮርዳኖስ ዓባይ ለአንድ ዓመት ክለቡን እንዲያሰለጥን ተሹሟል፡፡ ዮርዳኖስ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ወደ አሰልጣኝነቱ በመግባት በናሽናል…

18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሬጎን የሚካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል። በውድድሩ ÷ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች በአጠቃላይ 40 ማለትም 21 ወንድና 19 ሴት አትሌቶችን እንደምታሳትፍ ተገልጿል። አትሌቶቹ በ800 ሜትር፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል፣ በ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር እንዲሁም…

 ዱሬሳ ሹቢሳ ባህር ዳር ከነማን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት በይፋ የዝውውር ገበያውን የተቀላቀለው ባህር ዳር ከተማ የመስመር አጥቂውን ዱሬሳ ሹቢሳን በሁለት ዓመት ውል ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ ከአዳማ ወጣት ቡድን የተገኘው ዱሬሳ ሹቢሳ ያለፈውን እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ ማሳለፉ ይታወሳል። አሁን ዳግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ አብርሃም መብራቱ ጋር…

ሲዳማ ቡና ወንድማገኝ ተሾመን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲዳማ ቡና በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ክለቡን ሲመራ የነበረውን ወንድማገኝ ተሾመን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙን አስታወቀ፡፡ ከረዳት ወደ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት በመምጣት ክለቡ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ ተቀምጦ እንዲያጠናቅቅ ያስቻለው አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ÷ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሲዳማ…

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በአሜሪካ ኦሬገን በሚካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክለው የአትሌቲክስ ቡድን በዛሬው ዕለት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት÷ ዛሬ ምሽት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለቡድኑ መልካም እድል ተመኝተው…