Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ መከላከያ እና ፋሲል ከነማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መከላከያ ሲዳማ ቡናን 5 ለ 3 አሸንፏል፡፡ ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት በተካሄደው እና ስምንት ጎሎችን ባስተናገደው ጨዋታ መከላከያ ከባህርዳር ስታዲየም ወሳኝ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል፡፡ ለመከላከያ ተሾመ በላቸው ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፥ ቢኒያም በላይ፣ አዲሱ ቱሳ እና ክሌመንት ቦዩ ቀሪ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ ለሲዳማ ቡና አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን፥ ዳዊት ተፈራ ቀሪዋን አንድ ጎል…
Read More...

አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ከቀናት በኋላ በዩጋንዳ አስተናጋጅንት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የሴካፋ ሴቶች እግርኳስ ውድድር ላይ ሉሲዎቹ በአሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል የሚመሩ ይሆናል፡፡ አሰልጣኝ ፍሬው ከ20 ዓመት በታች የሴቶቹን ብሔራዊ…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የግብፅ አቻውን በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በማላዊ ቢንጉ ስታዲየም እንዲካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወስኗል፡፡ ቀደም ሲል ለኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የተመረጠው የባህርዳር ስታዲየም የካፍ ደረጃን ባለማሟላቱ ካፍ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምታደርገውን ጨዋታ በሌላ ሀገር ስታዲየም እንድታደርግ…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፐሪሚየር ሊግ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጥሏል፡፡ ፈረሰኞቹ ረፋድ 4 ሰዓት በባህርዳር ስታዲየም ከወላይታ ዲቻ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የነጥብ ልዩነቱን ለማጥበብ እና ወደ ዋንጫ ፉክክር ለመመለስ የፋሲል ከነማ…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ ትሳተፋለች፡፡ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትሮች እንዲሁም በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በ2022 የቫሌንሺያ ማራቶን ላይ እንደምትሳተፍ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። አትሌቷ…

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡   ረፋድ 4 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ከባህርዳር ስታዲየም ማግኘት ችሏል፡፡   ለድሬዳዋ ከተማ ሄኖክ…

ዋልያዎቹ የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ግንቦት 25 ቀን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርግባቸው ቀናት ይፋ ሆነዋል፡፡ የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች በዚህ ወር መካሄድ የሚጀምሩ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ 2 ጨዋታዎችን የምታደርግበት ቀናት ታውቀዋል፡፡ በምድብ መ ከግብፅ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር…