Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አቡበከር ናስር የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሙያተኞች ማኅበር የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስርን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች አድርጎ መምረጡን አስታወቀ። ለመጀመሪያ ጊዜ የዓመቱን ኮከብ የመረጠው ማኅበሩ በቀጣይ የሚዘጋጅ የሽልማት ሥነ-ስርዓት እንደሚኖረው መግለጹን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሃዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ሃዲያ ሆሳዕናን 2ለ1 አሸንፏል። ለኢትዮጵያ ቡና አቡበከር ናስር በ 2ኛው እና በ75ኛው ደቂቃ ላይ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ለሃዲያ ሆሳዕና ብቸኛዋን ጎል በ43ኛው ደቂቃ ላይ ደስታ ዋሚሾ ማስቆጠሩን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ጅማ አባ ጅፋርን 4ለ 1 አሸንፏል። ለሲዳማ ቡና ኦኪኪ አፎላቢ በ6፣ 38 እና 71ኛው ደቂቃ ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ አራተኛውን ጎል ይገዙ ቦጋለ አስቆጥሯል። ለጅማ አባጅፋር ብቸኛዋን ጎል በ70ኛው ደቂቃ ተመስገን ደረሰ አስቆጥሯል ። የሲዳማ ቡናን ማሸነፍ…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ያረጋገጠውን አዳማ ከተማ በሳላሀዲን ሰይድ  እና አማኑኤል ተርፋ ግቦች ማሸነፍ ችሏል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…

ፋሲል ከነማ  የአሸናፊነት ዋንጫውን  ዛሬ ሃዋሳ ላይ ተርክቧል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 ዓ.ም የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ዛሬ ሐዋሳ ላይ ተረክቧል። በ25ኛው ሳምንት በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ ከሐዋሳ ከተማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ለፋሲል ከነማ  ዓለምብርሃን ይግዛው በ31ኛው…

በፕሪሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ ወልቂጤ ከተማን 1ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰበታ ከተማ ወልቂጤ ከተማን  1ለ 0 አሸነፈ። የሰበታ ከተማን የማሸነፊያ ጎል ቶማስ ምህረቱ በራሱ ግብ ላይ በ81ኛው  ደቂቃ ላይ  ማስቆጠሩን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ዲቻ ባህርዳር ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ዲቻ ባህርዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ። የወላይታ ዲቻን ማሸነፊያ ግቦች በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጥሩ ብቃት እያሳየ የሚገኘው ወጣቱ ተጫዎች ቸርነት ጉግሳ በ55ኛ እና 76ኛው ደቂቃዎች ላይ ማስቆጠሩን ሰኮር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን…