Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማሊ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማሊ ቡርኪና ፋሶን 2ለ1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ማሊ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
Read More...

የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታላቁ ሩጫ አስታወቀ። ውድድሩ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ስያሜ በመቀየር "የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን" በሚል ይካሄዳል ነው የተባለው። በዘንድሮው ውድድር ከወትሮው በተለየ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ፣ ጆርጂያ፣…

ኬፕ ቨርዴ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ኬፕ ቨርዴ ሞሪታኒያን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡ ምሽት 2 ሰዓት በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሪያን ሜንዴዝ ባለቀ ደቂቃ ባስቆጠራት የፍጹም ቅጣት ምት 1 ለ 0 አሸንፋለቸ፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ኬፕ ቨርዴ በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ሃድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንተነህ ተፈራ በ33ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ…

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ በመቀሌ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገር አቀፍ የችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመቀሌ ከተማ ተከሂዷል። በችቦ ቅብብሎሽ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል። መርሐ-ግብሩ በመጪው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው…

አንጎላ ናሚቢያን በማሸነፍ  ሩብ ፍጻሜው ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አንጎላ ናሚቢያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ገብታለች፡፡ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በቡዋኬ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አዲልሰን ነቡላ፣ ጊልሰን ዳላ እና ኦገስቲኖ ሙቡሉ ለአንጎላ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡ በጨዋታው የአንጎላው ግብ ጠባቂ አዲልሰን ኔብሉ እና የናሚቢያው…

ቅዱስ ጊዮርጊስ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳይጠበቅ በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኤፍሬም አሻሞ፣ ቻርለስ ሙሲጌ እና ሱራፌል ጌታቸው የድሬዳዋን ጎሎች አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ድሬዳዋ ነጥቡን 14 በማድረስ ለጊዜው 10ኛ ደረጃ ላይ…