Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሥምምነት ፈጸሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሃይሌ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾመዋል። አሰልጣኝ ገብረ መድህን በዛሬው ዕለት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝነት ሥምምነት መፈጸማቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ አሰልጣኙ ለአንድ ዓመት ውል በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ መድንን ክለብ ሳይለቁ ደርበው የሚሰሩ ይሆናል።
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡናን የገጠመው ሀዋሳ ከተማ በእዮብ አለማየሁ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ በ9 ነጥቦች 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ÷ተሸናፊው ሲዳማ ቡና …

የ2023 የአፍሪካ እጩ ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የአፍሪካ እጩ ኮከብ ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ በምርጫ ዝርዝሩ ውስጥ 30 ተጫዋቾች በእጩነት የቀረቡ ሲሆን÷ 20 የሚሆኑት በአፍሪካ ክለቦች የሚጫወቱ ናቸው ተብሏል፡፡ በእጩ ዝርዝሩ ሞሃመድ ሳላህ፣ሪያድ ማህሬዝ፣አሺራፍ ሀኪሚ፣ሞሃመድ ኩዱስ፣ቪንሴንት አቡበከር፣ሳዲዮ…

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 1ኛ ዙር የውድድር መርሐ- ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት አንደኛ ዙር የውድድር መርሐ- ግብር ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሕዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጅማ አባጅፋር እና ወልዲያ ከተማ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚጀመር ከወጣው መርሐ- ግብር ለማወቅ…

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ እና መቻል ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 5ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። 9 ሰአት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የአዳማ ከተማን ግቦች አብዲሳ ጀማል እና አሰጋኸኝ ጴጥሮስ (በራሱ ላይ) ሲያስቆጥሩ ዘርዓይ ገብረስላሴ ደግሞ የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ…

ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር ይካሄዳል። ጨዋታው ምሽት 12፡10 ላይ በአቡጃ አቢዮላ ስታዲየም የሚደርግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ከቀናት በፊት…

ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ የ2023 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡ የ2022/ 2023 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ- ሥርዓት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በወንዶች አርጀንቲናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡…