Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኮሚቴው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ትናንት ባደረገው ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡ በ28ኛ ሣምንት ፕሪሚየር ሊግ የተደረጉ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ ነው ኮሚቴው ውሳኔ ያሳለፈው፡፡ በውሳኔው መሠረትም ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በእኩል ሰዓት በተለያየ ሜዳ ይደረጋሉ፡፡ በመሆኑም÷ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም እንዲሁም ወላይታ ድቻ…
Read More...

ዋሊያዎቹ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በመጓዝ የወዳጅነት እና የልምድ ልውውጥ ጨዋታዎችን ሊያደርግ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው÷የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከካረቢያኑ ጉያና ብሄራዊ ቡድን ጋር ሐምሌ 26 በዋሺንግተን ዲሲ ሴግራ ፊልድ ስታዲየም እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ሐምሌ 29 ከትላንታ…

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደውየ28ኛ ሣምንት መርሐ ግብር÷ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውተዋል፡፡ በተጠባቂው ደርቢ ጨዋታም ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ1 በሆነ…

በሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና አትሌት ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ። 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ተብሎ የሚጠራው ቦታ መነሻና መድረሻው አድርጎ ተካሂዷል፡፡ በማራቶን ውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃኑ ነበበው…

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኋላ ዛሬ ይመለሳል፡፡ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚካሄደው የ28ኛ ሣምንት መርሐ ግብር÷ 9፡00 ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡ 12፡00 ላይ ደግሞ ባሕርዳር ከነማ ከሲዳማ ቡና እንደሚጫወቱ…

39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር መካሄድ ጀምሯል፡፡ ውድድሩ እየተካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበበባ ሲሆን÷ መነሻ እና መድረሻውን ሰሚት ማድረጉም ተገልጿል፡፡ በውድድሩ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ እየተሳተፉ ነው፡፡ ለውድድሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ…

39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ መነሻ  እና መድረሻውን  ሰሚት  በሚያደርገው የማራቶን ውድድር ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ይካፈሉበታል። ለውድድሩ…