Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በመቀሌ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚሳተፉበት የ2015 የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል። ውድድሩን የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ሃይሌና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ልማት ሽግግር ሃላፊ ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) አስጀምረዋል። አቶ ወንድሙ ሃይሌ ከሰኔ14 እስከ 18 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄደው ውድድር የህዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነትን የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል። ውድድሩ በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያን ወክለው በዓለም…
Read More...

የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድሮች ተከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተጀመረው 3ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተለያዩ ርቀቶች የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውነዋል፡፡ በዚሁ መሰረት በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር÷ አቤል በቀለ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ ኃይሌ ጥጋቡ ከደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እንዲሁም አንዳርጋቸው…

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ በመሰለፍ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት ስሙ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል፡፡ ሮናልዶ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሀገሩ ፖርቹጋል አይስላንድን በገጠመችበት ጨዋታ 200ኛ ጨዋታውን ለብሄራዊ ቡድኑ አድርጓል፡፡ በጨዋታውም ግብ አስቆጠሮ ሀገሩን አሸናፊ ማድረግ መቻሉ ነው…

ኢትዮጵያ እና ማላዊ በአቻ ውጤት ተለያ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ማላዊ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር አከናውኗል፡፡ የሁለቱ አገራት ጨዋታ በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡…

ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ከማላዊ አቻው ጋር እያካሄደ ነው፡፡ ጨዋታው በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በምድብ 4 የማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ያለችው…

ቼልሲ ንኩንኩን ሲያስፈርም አርሰናል ለራይስ 90 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በቀጣዩ ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር በስፋት እየተሳተፉ ነው። በተለይም የዝውውር መስኮቱ የተከፈተላቸው የእንግሊዝ ክለቦች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲሆን÷ በዚህም ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩን ከአር ቢ ሌፕዚግ አስፈርሟል። ንኩንኩ ክለቡን ለተረከቡት አሰልጣኝ…

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣዩ ዓመት ፋሲል ከነማን ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ የጀመረው ፋሲል ከነማ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለ ሲሆን÷ በ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ክለቡ በዘንድሮው…