Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል ወልቂጤ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ዛሬ 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ምንይሉ ወንድሙ እና ግሩም ሀጎስ ለመቻል ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡ በሌለ በኩል÷ከምሽቱ12 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷል የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ እና የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በቱርኩ አታቱርክ ኦሎምፒክ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ ኢንተርሚላን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአውሮፓ…

ለሀምበርቾ እግር ኳስ ቡድን 2 አውቶብሶች እና የ250 ሺህ ብር ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ከልል መንግስት ክልሉን ወክሎ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለተቀላቀለው የሀምበርቾ እግር ኳስ ቡድን የተለያዩ ማበረታቻዎችንና የእውቅና ሰርተፊኬት አበርክቷል። በመርሐ ግብሩ የተገኙት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ርስቱ ይርዳ የክልሉን ስፖርት ለማሳደግ መንግስት አበክሮ እየሰራ…

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ቡድኖቹ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ዛሬ ያደረጉት የ26ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች…

አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለሜቻ ግርማ በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር  የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸንፏል፡፡ አትሌት ለሜቻ ርቀቱን በ7 ደቂቃ 52 ሰከንድ 11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ክብረ ወሰን በመስበር ያሸነፈው፡፡ በዚህም በኬንያዊው አትሌት በ7 ደቂቃ 53 ሰከንድ 63 ማይክሮ ሰከንድ…

የሀድያ ሆሳዕና እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ 3ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ጥሩ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ 3 ለ 0 እየመራ ቢቆይም ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ መጋራት ችሏል። በጨዋታው የአዳማ ከተማን ሁለት ግቦች ዳዋ ሆቴሳ ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ አዲስ…

የስድስት ሀገራት አትሌቶችን የሚያሳትፈው የአስመራ ማራቶን የፊታችን እሑድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ጨምሮ የስድስት ሀገራት አትሌቶችን የሚያሳትፈው የአስመራ ማራቶን በመጪው እሑድ እንደሚካሄድ የኤርትራ ባህልና ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኤርትራ ባህልና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ ÷በውድድሩ መርሐ ግብር የወንዶች ሙሉ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድርመዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡…