Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና በፈፀሟቸው የዲሲፕሊን ጥሰቶች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ በ3ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በክለብ ደረጃ ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ3ኛ ሳምንት ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ክለቡ 5 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኗል፡፡…
Read More...

የፕሪሚየር ሊጉ ሁለት መርሐ ግብሮች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ አዳማ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ እንዲሁም ኢትጵያ ቡና ከባህር ዳር ከተማ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡ ለአዳማ ከተማ አብዲሳ ጀማል እና ዮሴፍ ታረቀኝ እንዲሁም ለሀምበሪቾ ዱራሜ በፍቃዱ አስረሳኸኝ እና ዳግም በፍቃዱ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ በውጤቱ መሰረት አዳማ ነጥቡን ወደ 5…

አውስትራሊያዊቷ ዋናተኛ በጀርባ ዋና ስፖርት የዓለም ክብረወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው ዓለም አቀፍ የዋና ስፖርት ውድድር አውስትራሊያዊቷ ዋናተኛ ኬይሊ ማክዊን የጀርባ ዋና የዓለም ክብረወሰንን ሰብራለች፡፡ ኬይሊ ማክዊን 50 ሜትሩን የዋና ርቀት ለማጠናቀቅ 26 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባታል፡፡ በዚህም በቻይናዊዋ አትሌት ሊዩ ዥያንግ በ2018 ተይዞ የነበረውን…

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሽያ ግማሽ ማራቶን ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቫሌንሽያ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ በግማሽ ማራቶን ውድድሩ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ ሀጎስ ገብረህይወት እና ሰለሞን ባረጋ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህም አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት2ኛ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ 3ኛ እንዲሁም ሰለሞን ባረጋ 4ኛ ደረጃን…

ቼልሲ እና አርሰናል 2 ለ2 ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛው ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ የነበረው የአርሰናልና ቸልሲ ጨዋታ በ2 አቻ ተጠናቋል፡፡ የቼልሲን ጎሎች ኮል ፓልመር እና ሚሃየሎ ሙድሪክ ሲያስቆጥሩ ፥ ለአርሰናል ደግሞ ዴክላን ራይስ እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ የአቻ ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 0…

ማንቸስተር ሲቲ ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሜዳው ብራይተንን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። በዚህም ነጥቡን 21 በማድረስ የደረጃ ሰንጠረዡ ለጊዜው እየመራ ይገኛል። በሌላ ጨዋታ ከሜዳው ውጪ በርንማውዝን የገጠመው ዎልቭስ በተመሳሳይ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፎ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።…

ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ። ለሊቨርፑል የማሸነፊያ ጎሎቹን ሞሀመድ ሳላህ ከእረፍት በኋላ በፍጹም ቅጣት ምት እና በጨዋታ አስቆጥሯል። በጨዋታው ያሸነፈው ሊቨርፑል በ9 ጨዋታ 20 ነጥብ በመሰብሰብ የደረጃ ሰንጠረዡ ለጊዜው እየመራ…