Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የደልሂ ግማሽ ማራቶን በአትሌት አልማዝ አያና አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ በተካሄደው 18ኛው የደልሂ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር አትሌት አልማዝ አያና አሸነፈች፡፡ ርቀቱን ለማጠናቀቅም 1 ሰዓት ከ 7 ደቂቃ ከ59 ሰከንድ ፈጅቶባታል። አትሌቷ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ ውድድር ተመልሳ ያስመዘገበችው ውጤት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የ2016 የሪዮ ኦሎምፒክ አሸናፊዋ አትሌት አልማዝ አያና ከ6 ዓመታት በፊትም በደልሂ በተካሄደ ተመሳሳይ የግማሽ ማራቶን ውድድር ማሸነፏ ይታወሳል፡፡ #Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን…
Read More...

ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ወልቂጤ ከተማና ሲዳማ ቡና 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ የወልቂጤ ከተማን ግብ በተጨማሪ ደቂቃ ተመስጌን በጅሮንድ…

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። ቀደም ብሎ በተካሄደውና ሀምበሪቾ ዱራሜን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባገናኘው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ 2 ለ 1 አሸንፏል። አቤል ያለው እና አማኑኤል ኤርቦ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ…

ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁለተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬዳዋን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በጫላ ተሽታ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 6 በማድረስ ሊጉን በበላይነት መምራት ጀምሯል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ምሽት 12…

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይና ትዕግስት አሰፋ የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ትዕግስት አሰፋ የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት እጩ  ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ፡፡ የአለም አትሌቲክስ የ2023ቱ የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት የ11 እጩዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ውድድር የ10 ሺህ ሜትር ሴቶች አሸናፊዋ እና የዳይመንድ ሊጉ ባለ ሪከርድ ጉዳፍ ፀጋይ እና በበርሊን…

ኤዲን ሃዛርድ ጫማ ሠቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ ተጫዋች ኤዲን ሃዛርድ በ32 ዓመቱ ራሱን ከእግርኳስ ማግለሉን አስታወቀ፡፡ ሃዛርድ÷ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ ባጋጠሙት ተደጋጋሚ ጉዳቶች የመሰለፍ ዕድል ማጣቱ ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳን ቀሪ የኮንትራት ጊዜ ቢኖረውም ከማድሪድ ጋር በስምምነት መለያየቱን ነው የገለጸው፡፡…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች  ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንደኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ይፋ ሆነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ በሳምንቱ በተደረጉ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል። በዚህም የሀዋሳ ከተማው ተጫዋች በረከት…