Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአዲዳስ ኩባንያ ጋር ትልቁን የመለያ ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ ጋር ለቀጣይ 10 ዓመታት ተጨማሪ ውል መፈራረሙን አስታወቀ። በውሉ መሰረትም ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር ያላው የውል ሥምምነት እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 2035 ድረስ ይቆያል ነው የተባለው፡፡ በዚህም የላንክሻየሩ ክለብ ከኩባንያው ለ10 አመት የሚቆይ የ900 ሚሊየን ፓውንድ የመለያ ሥምምነት የተፈራረመ ሲሆን፥ ይህም የፕሪሚየርሊጉ ትልቁ የመለያ ገቢ በመሆን ተመዝግቧል፡፡ የክሉቡ…
Read More...

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ። ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም ጋር የተደለደሉት ፈረሰኞቹ ÷ ነገ ቢሾፍቱ በሚገኘው ክብር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ታውቋል። ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነሐሴ 12 ወይም 13/2015 ዓ.ም…

ኢትዮጵያ ቡሩንዲን 2 ለ 0 ረታች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋ ቡሩንዲን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ እሙሽ ዳንኤል በመጀመሪያው እና በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ጎሎች ነው ኢትዮጵያ ተጋጣሚዋን የረታችው፡፡ የሴካፋ ሴቶች ከ 18 ዓመት በታች ውድድር በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ…

የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ከ20 አመት በታች የ100 ሜትር ሩጫ ክብረ ወሰን ተሰበረ። ክብረ ወሰኑን በደቡብ አሜሪካ ከ20 አመት በታች የአትሌቲካስ ሻምፒዮና ላይ፥ የሱሪናሙ አትሌት ኢሳማዴ አሲንጋ 9 ሰከንድ ከ89 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሻሽሎታል። የብራዚሉ ኤሪክ ካርዶሶ እና የኮሎምቢያው…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ አሜሪካ ያቀናል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ በነገው እለት ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ የዋሊያዎቹ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን  እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ  ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማሪያም  ጋዜጣዊ መግለጫ…

ተደጋጋሚ ጉዳቶችና የሜዳ ላይ አቋም መቀነስ እግር ኳስ እንዳቆም አስገድደውኛል  – ሳላዲን ሰይድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተደጋጋሚ ጉዳቶችና የሜዳ ላይ አቋም መቀነስ እግር ኳስ እንዳቆም አስገድደውኛል ሲል አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ተናገረ፡፡ ሳላዲን እግር ኳስ የማቆሙ ዜና ከተሰማ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ እግርኳስ ያቆመበትን ምክንያት ያስረዳው ሳላዲን÷ ከጉዳት ጋር በሚያጋጥመው የጤና…

ዴቪድ ሲልቫ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የመሀል ክፍል ተጫዋች ዴቪድ ሲልቫ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ራሱን አግልሏል፡፡ የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ ባለውለታ ዴቪድ ሲልቫ ከከባድ የቁርጭምጭሚት ጉዳት በኋላ ነው ከኢንተርናሽናል እግር ኳስ ራሱን እንዳገለለ ያስታወቀው፡፡ ሲልቫ በፈረንጆቹ 2010 ከስፔኑ ቫሊንሲያ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለ ሲሆን÷ ከቡድኑ…