Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለአትሌቲክስ ቡድኑ አቀባበል አድርገዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ሌሎችም የፌዴሬሽን አመራሮች በመገኘት ለአትሌቶቹ አቀባበል እንዳደረጉላቸው…
Read More...

ኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ ሊሰራበት ይገባል – የቦክስ ስፖርተኞች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በቦክስ ስፖርት ወርቅ ያስገኙት ስፖርተኞች ተናገሩ፡፡ የቦክስ ባለወርቆቹ ቤተልሄም ገዛኸኝ እና ቤተል ወልዴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ከዓመታት ቆይታ በኋላ በሴቶች የቦክስ…

አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርሴናል በ65 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሲቲ ደግሞ በ64 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ቀደም ሲል ብራይተንን 2 ለ 1 ያሸነፈው ሊቨርፑል በ67…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬደዋ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ድሬደዋ ከተማ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቸኛ ግብ ሲሞን ፒተር ሲያስቆጥር÷የድሬደዋ ከተማን ደግሞ ቻርልስ ሙሲጌ አስቆጥሯል፡፡

ሊቨርፑል የሊጉን መሪነት ተረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሊቨርፑልን የማሸነፈያ ግቦች ሉዊስ ዲያዝ እና ሞሃመድ ሳላህ አስቆጥረዋል፡፡ ብራይተንን ከሽንፈት ያላደነችውን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዳኒ ዌልቤክ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን…

ዛሬ ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱን ተጠባቂ ጨዋታ ያስተናግዳል። የሊጉ 30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲካሄዱ መሪዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን የያዙት ክለቦች የሚያካሂዱት ጨዋታ ይጠበቃል። ሊጉን 64 ነጥብ በመያዝ እየመራ የሚገኘው አርሴናል 63 ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ…

ኢትዮጵያ የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በሁለተኝነት አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 45ኛውን የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ ኪሎ ሜትር ውድድሮች የተሳተፈች ሲሆን 2 ወርቅ፣6 ብር እና 2 ነሃስ…