Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በወጣት ሴቶች የ6 ኪሎ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት አሸንፈዋል፡፡ በዚህም ማርታ አለማየሁ አንደኛ፣አሳየች አይቸው ሁለተኛ እንዲሁም ሮቤ ዲዳ ሶስተኛ ሆነው በመግባት የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል፡፡ በተመሳሳይ በወጣት ወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዝገበ ስሜ የብር ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡
Read More...

 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በሰርቢያ ቤልግሬድ ይካዳል፡፡ በውድድሩ ከ51 ሀገራት የተውጣጡ ከ45 በላይ አትሌቶች÷ በወጣቶች እና በአዋቂ በአምስት የውድድር ዘርፎች ይሳተፋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 6 ሠዓት ከ 35 ደቂቃ ላይ በሚካሄደው የ8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች የሩጫ ውድድር…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ሙሴ ኪሮስ በ6ኛው ደቂቃ እና ቢኒያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል። ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት ያላዳነችውን ጎል…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ አዳማ ከተማ ሙሴ ኪሮስ በ6ኛው ደቂቃ እና ቢኒያም አይተን በ54ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥቷል። ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት…

አማኑኤል ገብረሚካኤል በጉዳት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የፋሲል ከነማው አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ገለጹ፡፡ በውድ የዝውውር ገንዘብ ፋሲል ከነማን የተቀላቀለው አማኑኤል÷ ክለቡ ትላንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ በተለያየበት ጨዋታ ከግብ ጠባቂው ጋር በመጋጨቱ ነው…

ከእግርኳስ ሜዳ ስለምለያይበት ጊዜ አስቤ አላውቅም – ሊዮኔል ሜሲ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በአሁኑ ወቅት ለኢንተርሚያሚ እየተጫወተ ይገኛል። ከወራት በኋላ 37ኛ ዓመቱን የሚይዘው ሊዮኔል ሜሲ ከቢግ ታይም ፖድካስት ጋር ባደረገው ቃል ምልልስ፤ የእድሜው መግፋት በእግርኳስ ህይወቱ ላይ የሚያመጣው ጫና እንደሌለ ተናግሯል። በመሆኑም በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ስለሚያስመዘግበው ስኬት…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የባህርዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ እንዳስታወቀው፤ አለልኝ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተለይቶ በትውልድ ስፍራው አርባ ምንጭ ለእረፍት የሄደ ሲሆን ትናንት ምሽት በድንገት ህይወቱ አልፏል።…