Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ሪከርድ በማሻሻል ጭምር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ የቦታውን ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸንፏል፡፡ አትሌቱ 28:34 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የቦታውን ሪከርድ ጭምር በማሻሻል መሸነፍ የቻለው፡፡ በተመሳሳይ በቱርክ ኢስታንቡል በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ፀሐይ ገመቹ 1:05:52 በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር አትሌት በቀለች ጉደታ 1:06:35 በሆነ ሰዓት በመግባት ሦስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን…
Read More...

ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ በወንዶች የሮም ማራቶን አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሮም የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያዊው ፍቅሬ በቀለ አዲስ ክብረ ወስን በማስመዝገብ አሸነፈ፡፡ አትሌቱ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት አዲስ ክብረ ወሰን የሰበረ ሲሆን፥ ኬንያዊው ቤንጃሚን ኪፕቶ በ2009 ያስመዘገበውን ሪከርድ በመሰበር ነው ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀው። አትሌት ታደሰ ማሞ ውድድሩን…

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ሊግ ሲጫወት የቆየው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን መቀላቀሉን አረጋግጧል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ጌዲዮ ዲላን ያስተናገደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዳልካቸው ይልቃል እና አቤል ሀብታሙ ባሰቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ የዛሬ ረፋዱን ውጤት ተከትሎም ኢትዮ ኤሌክትሪክ…

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር የሚያደርገውን የመልስ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ያከናውናል። በአሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ ምሽት 12 ሰዓት ለሚካሄደው የመልስ ጨዋታ ወደ አክራ በማቅናት ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም…

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው አዳማ ከተማ የ60 ሚለየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዳማ ከተማ ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር የ60 ሚለየን ብር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ የሆነው አዳማ ከተማ ከአንበሳ ቢራ እና ዋሊን ቢራ አምራች ኩባንያ ጋር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል ። የስፖንሰር ሺፕ ስምምነቱ የአምስት ዓመት መሆኑን…

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከኮሞሮስ አቻው ጋር ነገ የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከኮሞሮስ አቻው ጋር ነገ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ ተገለጸ። የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ 10 ሺህ 725 ተመልካቾች በሚያስተናግደው “ስታድ ኦምኒስፖርትስ ደ ማሉንዚ” ይካሄዳል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን…

51ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን መጋቢት 19 ጀምሮ በሃዋሳ ይካሄዳል

  አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጋቢት 19 እስከ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።   በሻምፒዮናው ላይ የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ የክለቦችና በአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት የሚገኙ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።…