Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በበርሊን የሴቶች ማራቶን ክብረወሰን ለሰበረችው አትሌት ትዕግስት አቀባበል ተደረገላት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ49ኛው የበርሊን ሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰንን በማሻሻል ላሸነፈችው አትሌት ትዕግስት አሰፋ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎላታል። አትሌቷ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ስትገባ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውላታል። በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የአበባ ጉንጉን ተበርክቷል። በ49ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2 ሰዓት11…
Read More...

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከብሩንዲ ጋር አድርጓል፡፡ ሉሲዎቹ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በመለያ ምት 5 ለ…

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳሱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮችና ስራ አስፈፃሚ አባላት ጋር በእግር ኳሱ ዕድገት…

በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተጫወተው ሃድያ ሆሳዕና በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል። በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በመለያ ምት 5 ለ…

የሰሜን ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር ያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ በወሰደብት የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ክርስቲያን ሮሜሮ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን ቶተንሃምን አቻ አድርጎ የመጀመሪያውን አጋማሽ አንድ አቻ አጠናቅቀዋል፡፡…

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው። ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው…

ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ሲቲ÷ ፊል ፎደን እና ኤርሊንግ ሃላንድ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡ ሮድሪ በ46ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ክርስታል ፓላስ…