Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አርሰናል ከ6 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ያደርጋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ከኔዘርላንድሱ ፒኤስ ቪ ኢንድሆቭን ጋር ዛሬ ምሽት ያደርጋል፡፡ አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ በመድረኩ ተሳትፎ ያደረገው በፈረንጆቹ 2017 ሲሆን÷ በዚህም በጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ ከምድብ ተሸንፎ መሰናበቱ የሚታወስ ነው፡፡ በማይክል አርቴታ ፊታውራሪነት የሚመሩት መድፈኞቹ ባለፈው ዓመት ባሳዩት ድንቅ እንቅስቃሴ የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ ከመሆናቸው ባለፈ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ማግኘት…
Read More...

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀናው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል። ባህር ዳር ከተማ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 0 አሸንፏል። የድል ጎሎቹን ሀብታሙ ታደሰ ከእረፍት በፊት እና በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥሯል። የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ የሚካሄድ…

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ (jks) የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ በዱባይ እየተካሄደ ባለው የእስያ አፍሪካ ዋንጫ የjks የካራቴ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት ሶስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያ አግኝተዋል። በመድረኩ በ60 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ናትናኤል…

ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል  ድል ሲቀናቸው ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳቸው ውጪ የተጫወቱት ማንቼስተር ሲቲና ሊቨርፑል ድል ሲቀናቸው በሜዳው የተጫወተው ማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሊቨርፑል ወልቨርሃምፕተን ወንደረርስንን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲረታ÷ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከሜዳው ውጪ ሶስት ነጥብ ይዞ…

በሞሮኮና ሊቢያ በአደጋ ህይወታቸው ያለፉትን ለመዘከር ተጫዋቾች ጥቁር ባጅ ያደርጋሉ – ፕሪሚየር ሊጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ የመሬት መንቀጥቀጥና በሊቢያ የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለመዘከር የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉም ተጨዋቾች ጥቁር ባጅ በክንዳቸው ላይ እንዲያደርጉ መወሰኑን ሊጉ አስታውቋል፡፡ የእንግሊዝ ፕረሚየር ሊግ በማህበራዊ ትስስር ገፁ÷ በቅርቡ በሞሮኮ እና በሊቢያ በተከሰቱት  አሳዛኝ  የተፈጥሮ…

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የፊታችን ጥቅምት 17 ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የፊታችን ጥቅምት 17 ቀን እንደሚጀመር ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ፌደሬሽኑ የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበትን ቀን እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ መሰረትም የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብሩ…

ፍቅረማሪያም ያደሳ በአፍሪካ ዞን የቦክስ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ በፍጻሜ ይጫወታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ቦክሰኛ ፍቅረማሪያም ያደሳ (ጊችሮ ነብሮ) በአፍሪካ ዞን የኦሊምፒክ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ ዛሬ በፍጻሜ ይጫወታል። ፍቅረማሪያም በዛሬው እለት በ57 ኪሎ ግራም ከናይጀሪያዊው ቦክሰኛ ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን ያደርጋል። በፍጻሜ ጨዋታው አሸናፊ መሆን ከቻለም ኢትዮጵያን በፓሪሱ ኦሊምፒክ ይወክላል። በሴኔጋል…