Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሴራሊዮን አቻው ጋር አከናውኗል፡፡ የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡ ጨዋታው በተከሰተ ጭጋጋማ አየር ምክንያት ለሶስት ጊዜ ተቋርጦ ነው የተጠናቀቀው። በተካሄደው የማጣሪያ ጨዋታም ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ…
Read More...

የፊፋ ዋና ፀሐፊ ለሥራ ጉብኝት ድሬዳዋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዋና ፀሐፊ ፋጡማ ሳሞራይ ለሥራ ጉብኝት ማምሻውን ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡ ዋና ፀሐፊዋ ማምሻውን ድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ዋና ፀሐፊዋ በድሬዳዋ ቆይታቸው የሕፃናት…

አትሌት ትዕግስት በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ውስጥ ተካትታለች፡፡ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ዘርፍ ቀደም ሲል 11 ዕጩዎች ለምርጫ የቀረቡ ሲሆን÷የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ ዝርዝር ውስጥም…

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2016 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብርን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡ በዕለቱም ልደታ ክፍለ ከተማ ከአርባ…

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ሲዳማ ቡና በይፋ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ላለፈው አንድ ዓመት ሲያሰለጥን የቆየው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከሲዳማ ቡና ጋር ተለያይተዋል። የሲዳማ ቡና ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እና ምክትላቸው ቾንቤ ገብረህይወት ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ…

በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በተደረገው ውድድር የቦታውን ሪከርድ በመስበር አሸነፉ፡፡ በቤይሩት ማራቶን በወንዶች ጋዲሳ ጣፋ 02፡10፡34 በመግባት የቦታውን ሪከርድ በማሻሻል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ጎጃም በላይነህ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡ እንዲሁም በሴቶች በተደረገው…

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ቡድን ማሊን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ቡድኑ ከሜዳው ውጪ ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ነው 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግቦች እሙሽ ዳንኤል እና ንግስት በቀለ አስቆጥረዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታውን የፊታችንእሑድ…