Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ለሜቻ የዳንኤል ኮመንን የ25 አመት ክብረ ወሰንን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ። አትሌት ለሜቻ ርቀቱን 7 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ከ81 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈው። ክብረ ወሰኑ በኬንያዊው ዳንኤል ኮመን ለ25 አመታት ተይዞ የቆየ ነበር። ኮመን በ7 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ከ90 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነበር ክብረ ወሰኑን ይዞ የቆየው።
Read More...

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡   በወንዶቹ ምድብ አብዲሳ ቶላ በ2:05:42 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ÷ደሬሳ ገለቴና ሃይማኖት አለው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።   በወንዶቹ ምድብ ኢትዮጵያዊያኑ…

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፖላንድ የአንድ ማይል ውድድር ሁለተኛውን ፈጣን ሰአት አስመዘገበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ትናንት ምሽት በፖላንድ ቶረን በተካሄደ የቤት ውስጥ የአንድ ማይል ውድድር የዓለማችን ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡ አትሌቷ ርቀቱን 4 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ስታጠናቅቅ ይህ ሰዓትም ከገንዘቤ ዲባባ በመቀጠል ሁለተኛው የዓለማችን ፈጣን ሰዓት ሆኖ…

ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በመጪው ቅዳሜ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ከተቋረጠበት የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና በሚያደርጉት የሸገር…

የ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ አትሌቶች የተሳተፉበት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ አሸናፊነት ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ በሁለቱም ጾታ በ218 ነጥብ 1ኛ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡ እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ ማሰልጠኛ ማዕከል…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል፡፡ የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል። ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ…

ተጠባቂው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ተራዝሟል ። በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰአት በ12ኛ ሳምንት የሊጉ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ለጊዜው ባልተገለፀ ምክንያት…