ባለ 99 ፎቅ ህንጻ አዲስ አበባ ዉስጥ ሊገነባ ነዉ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 30 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀድሞው በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም የሚሰየም  ባለ 99 ፎቅ ህንጻ  አዲስ አበባ ውስጥ በቻይናው ቹ ዋን ሁይ ኩባንያ  ሊገነባ ነው ፡፡

ይህ ግዙፍ ህንጻ አዲሱ የአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል  በሚገኝበት ቦታ አካባቢ ነው የሚገነባው ፡፡

ህንጻው  ለቢሮና ለሆቴል አገልግሎት ይውላል ተብሏል ፡፡

ህንጻውን የሚያስገነባው ድርጅት የግንባታ ቦታ ጥያቄውና  እቅዱ ከመንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግሯል ፡፡

ህንጻው ሲገነባም በአፍሪካ ረጅሙ  ህንጻ ይሆናል ተብሏል ፤ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ረጅሙ ህንጻ  በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስ በርግ የሚገኘዉ ባለ 50 ወለል ህንጻ ነዉ ፡፡

ህንጻዉ  ከ አራት አመታት በኋላም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

 

 

ምንጭ፡http://enr.construction.com

Comments

Name *
Submit Comment